እንወያይ፤ የኢትዮጵያ የመናገር ነጻነት ወዴት እያመራ ነው?
እሑድ፣ ሚያዝያ 12 2017ማስታወቂያ
አለምአቀፉ ድጋፍ ለጋዜጠኞች የተባለ ተቋም ሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፤ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2024 በኢትዮጵያ ከ40 በላይ ጋዜጠኖች መታሰራቸውን ይፋ አድርጓል። አለምአቀፍ የጋዜጠኞች ተከራካሪ ድርጅት ሲ ፒ ጄይ በበኩሉ ወደ 7 ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ገልጸዋል። አለምአቀፍ የጋጤጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅቶች በተለይ በለውጡ ማግስት «በኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ያልታሰረበት ዓመት» ብለው አወድሰው የነበረ ቢሆንም ከለውጡ ማግስት ባሉ ዓመታት እስከ ቅርቡ በሚያወጧቸው መግለጫዎች በጋዜጠኞች ላይ እስር፣ አስገድዶ መሰወርና ወከባ እንደሚደርስ በተደጋጋሚ ሪፖርት አድርገዋል። በርካታ ጋዜጠኞች ለስደት መዳረጋቸውን በማከል።
በጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የሚደርሱ እስርና ወከባዎች በኢትዮጵያ በቋፍ ላይ የነበረውን የፕረስ ነጻነት አደጋ ላይ እንደጣለው የሙያው ባለቤቶችና ተከራካሪዎች በየጊዜው ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኝሉ። በሙያው የተሰማሩ ጋዜጠኞች የሙያዊ ክህሎትና የሥነምግባር ችግሮች እንደሚስተዋሉም በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ። «የኢትዮጵያ የፕረስ ነጻነት ወዴት እያመራ ነው?» የዛሬ የውይይታችን ርዕስ ነው።
መሉ ውይይቱን ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር