Jump to content

ናይጄሪያ

ከውክፔዲያ

የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ
Federal Republic of Nigeria (እንግሊዝኛ)
Àpapọ̀ Olómìnira ilẹ̀ Nàìjíríà (ዮሩባ)
Jamhuriyar Tarayyar Najeriya (ሀውዛ)
Njíkötá Óchíchìiwù Naíjíríà (ኢግቦ)

የናይጄሪያ ሰንደቅ ዓላማ የናይጄሪያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Arise, O Compatriots
የናይጄሪያመገኛ
የናይጄሪያመገኛ
ናይጄሪያ በአረንጓዴ ቀለም
ዋና ከተማ አቡጃ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ
መንግሥት
{{{
ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
 
ሙሐማዱ ቡሐሪ
የሚ ኦሲንባጆ
ዋና ቀናት
1914 እ.ኤ.አ.

መስከረም ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም.
መስከረም ፳ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ.ም.
 
የሰሜንና ደቡብ ናይጄሪያ ውህደት
የነፃነት አዋጅ

የሪፐብሊክ ምሥረታ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
923,768 (32ኛ)

1.4
የሕዝብ ብዛት
የ2010 እ.ኤ.አ. ግምት
 
155,215,573[1] (8ኛ)
ገንዘብ ናይራ (₦)
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ 234
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .ng


ናይጄሪያ በይፋ የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ አገር ናት። በሕዝብ ብዛትም ከአፍሪቃ አንደኛ ናት። ከቤኒንቻድካሜሩንኒጄር ፣ እና ከጊኒ ባሕረ ሰላጤ ጋር ድንበር ትካለላለች። በናይጄሪያ ውስጥ ትልቁ ብሔሮች ሀውዛኢግቦ እና ዮሩባ ናቸው። ግማሹ ሕዝብ እስላም ሲሆን ሌላው ግማሽ ደግሞ የክርስትና እምነት ይከተላል። ትንሽ የሕዝቡ ክፍልም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል።

የሳይንስ ጥናት እንደሚያሳየው ናይጄሪያ ከ፱ሺህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ነዋሪዎች እንደነበሩባት ያሳያል።[2] በቤንዌ እና ክሮስ ወንዞች አካባቢ ያለው ሥፍራ የባንቱ ፍልሰቶች መነሻ እንደ ነበረ ይታመናል።

የናይጄሪያ ስም ከኒጄር ወንዝ ነው የተወሰደው። ናይጄሪያ በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ስትሆን ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ናት። የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። የዓለም አቀፍ ገንዘብ ፈንድ እንደሚገምተው የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በ2011 እ.ኤ.አ. በ8% ያድጋል።[3]

መንግሥት እና ፖለቲካ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሲሆን መንግሥቷ በአሜሪካ መንግሥት ላይ ነው የተመረኮዘው። የህግ አውጪው አካል አወቃቀር የዌስትሚኒስትር ሥርዓትን ይከተላል። በአሁኑ ጊዜ ጉድላክ ጆናታን ፕሬዝዳንት ናቸው። ፕሬዝዳንቱ ለሁለት የአራት ዓመት ጊዜ ሲያገለግል በሕዝቡ ነው የሚመረጠው።

የናይጄሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሁለት አካሎች አሉት። እነዚህም ሴኔት እና የተወካዮች ምክር ቤት ናቸው። ሴኔቱ 109 መቀመጫዎች ሲኖሩት እያንዳንዱ ክልል በሶስት አባሎች ይወከላል። የአቡጃ ርዕሰ አካባቢም አንድ ተወካይ አለው። የሴኔት አባላት በሕዝብ ይመረጣሉ። የተወካዮች ምክር ቤት 360 መቀመጫዎች ሲኖሩት የእያንዳንዱ ክልል ወካዮች በሕዝብ ብዛት ነው የሚወሰነው።

የውጭ ግንኙነቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ነፃነቷን በ1960 እ.ኤ.አ. ካገኘች በኋላ ናይጄሪያ ለአፍሪካ ነፃነትና ክብር መታገል ዋና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አድርጋለች። የደቡብ አፍሪካአፓርታይድ ሥራዓት በመቃወም ትልቅ ሚና ተጫውታለች።[4] በ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ናይጄሪያ ከእስራኤል ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራት ሲሆን እስራኤል የናይጄሪያ ፓርላማ ህንጻዎችን አሰርታለች።[5]

ናይጄሪያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች አገር ናት። በምዕራብ አፍሪካም ሆነ በአፍሪካ በጠቅላላ ትልቅ ተጽዕኖ አላት። በተጨማሪም እንደ ኤኮዋስ ያሉ የምዕራብ አፍሪካ የትብብር ድርጅቶች መሥራች ናች።

ከ1970ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ ናይጄሪያ ዋና የነዳች አምራች ስትሆን የኦፔክ አባል ሀገር ናት።

በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ናይጄሪያውያን በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ወደ አውሮፓሰሜን አሜሪካ እና አውስትራሊያ ተሰድደዋል። ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ናይጄሪያውያን በአሜሪካን እንደ ሚኖሩ ይገመታል።

የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ሀገሯን የመከላከል፣ የሀገሯን ፍላጎት የማስጠበቅ እና ፀጥታ አስጠባቂ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት። ሠራዊቱ የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይል አለው። ሠራዊቱ ከነፃነት ጀምሮ በሀገሯ ታሪክ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በተለያዩ ጊዜያት የውትድርና ጁንታዎች ሥልጣን በመያዝ አገሯን አስተዳድረዋል።

የናይጄራያ ሠራዊት በፀጥታ ጠባቂነት ደረጃ ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በላይቤሪያ (1997 እ.ኤ.አ.)፣ አይቮሪ ኮስት (ከ1997 እስከ 1999 እ.ኤ.አ. ) እና ሲየራ ሊዮን (ከ1997 እ.ኤ.አ. 1999 እ.ኤ.አ.) ተሰማርቷል።

ግብርና ናይጄሪያ በዋናነት ለአለም የምታቀርበው ምርቶች በተለይ ካካውጎማ ናቸው። እንዲሁም ፔትሮሊየም ከሚያቀርቡት አገራት 12ኛ ነች። በተጨማሪ፣ የመኪና ሥራ ድርጅት (ኢኖሶን ተሽከርካሪ መፈብረክ) ይኖራል።

መልከዓ ምድር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። የቆዳ ስፋቷ 923,768 ካሬ ኪ.ሚ. ሲሆን ከዓለም ፴፪ኛዋ ትልቅ ሀገር ናት። ድንበሯ 4,047 ኪ.ሜ. ርዝመት ሲኖረው ከቤኒን 773 ኪ.ሜ.፣ ኒጄር 1,497 ኪ.ሜ.፣ ቻድ 87 ኪ.ሜ.፣ ካሜሩን 1,690 ኪ.ሜ. ትዋሰናለች። በተጨማሪም 853 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ጠረፍ አላት።

በናይጄሪያ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ቻፓል ዋዲ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2,419 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ነው። የአገሯ ዋና ወንዞች ኒጄር እና ቤንዌ ሲሆን ወደ ኒጄር ደለል ይፈሳሉ።

የአመራር ክፍሎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ናይጄሪያ በሠላሳ ስድስት ክፍላገራት እና አንድ የፌዴራል ግዛት ተከፍላለች። እነዚህ ክፍላገራት ወደ ፯፻፸፬ የአካባቢ ግዛቶች ተከፍለዋል።

ስድስት የናይጄሪያ ከተሞች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉባቸው። እነዚህም ሌጎስካኖኢባዳንካዱናፖርት ሀርኮርት እና ቤኒን ከተማ ናቸው። ሌጎስ ከ፰ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲኖሩባት ከሣህራ በታች በአፍሪካ ትልቁ ከተማ ናት።

የክፍላገራት ዝርዝር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ናይጄሪያ ፴፮ ክፍላገራትና አቡጃ ፌዴራል ግዛት አሏት።
  1. አቡጃ
  2. አናምብራ
  3. እኑጉ
  4. አክዋ ኢቦም
  5. አዳማዋ
  6. አቢያ
  7. ባውቺ
  8. ባየልሳ
  9. ቤንዌ
  10. ቦርኖ
  11. ክሮስ ወንዝ
  12. ዴልታ
  13. ኢቦንዪ
  1. ኤዶ
  2. ኤኪቲ
  3. ጎምቤ
  4. ኢሞ
  5. ጂጋዋ
  6. ካዱና
  7. ካኖ
  8. ካትሲና
  9. ኬቢ
  10. ኮጊ
  11. ክዋራ
  12. ሌጎስ
  13. ናሳራዋ
  1. ኒጄር
  2. ኦጉን
  3. ኦንዶ
  4. ኦሱን
  5. ኦዮ
  6. ፕላቶ
  7. ሪቨርስ
  8. ሶኮቶ
  9. ታራባ
  10. ዮቤ
  11. ዛምፋራ

ፈዴራል ግዛት፦ አቡጃ

የሕዝብ ስብጥር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተ.መ.ድ. እንደ ሚገምተው የናይጄሪያ የሕዝብ ቁጥር በ2009 እ.ኤ.አ. 154,729,000 ነበር። የ2006 እ.ኤ.አ. ብሔራዊ ቆጠራ እንደ ሚያመለክተው ከሆነ የሕዝቡ ቁጥር 140,003,542 ነበር።

የሀውዛ ሰው የኢግቦ ሰዎች የዮሩባ ሰዎች

በናይጄሪያ ውስጥ ከ፪፻፶ በላይ ብሔሮች ይገኛሉ። ትልቆቹ ብሔሮች ፉላኒ ወይም ሀውዛዮሩባ እና ኢግቦ ናቸው። ከእነሱ ቀጥሎ ደግሞ ኤዶኢጃውካኑሪኢቢብዮኑፔ እና ቲቭ ይገኛሉ።

የናይጄሪያ፣ ካሜሩን እና ቤኒን የቋንቋ ካርታ

በናይጄሪያ ውስጥ የተቆጠሩት ቋንቋዎች ፭፻፳፩ ይሆናሉ። ከእነዚህም ውስጥ ፭፻፲ቹ መደበኛ ተናጋሪዎች አሏቸው። ሁለት ቋንቋዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ብቻ ነው የሚነገሩት። ዘጠኙ ደግሞ ተናጋሪ የሌላቸው የጠፉ ቋንቋዎች ናቸው።

ከእንግሊዝኛ በኋላ ዋናዎቹ ልሳናት ዮሩብኛሐውዝኛኢግቦኛ ናቸው።

  1. ^ "Country Comparison:: Population". CIA The World Factbook. 2010. Archived from the original on 2011-05-01. https://web.archive.org/web/20110501130938/https://www.cia.gov/library/publications/the-world-factbook/rankorder/2119rank.html?countryName=Nigeria&countryCode=ni&regionCode=af&rank=8#ni በ2010-11-27 የተቃኘ. 
  2. ^ McIntosh, Susan Keech, Current directions in west African prehistory. Palo Alto, California: Annual Reviews Inc., 1981. 215–258 p.: ill.
  3. ^ ":RenCap projects 8% growth for Nigeria in 2011". Independentngonline.com (2011-05-09). በ2011-05-28 የተወሰደ.
  4. ^ "Collins Edomaruse, how Obasanjo cut UK, US to size", by Andrew Young, This Day (Nigeria) -, July 20, 2006.
  5. ^ Golda. Elinor Burkett, p. 202.
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ናይጄሪያ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።