ባተን ሩዥ (እንግሊዝኛ፦ Baton Rouge) የሉዊዚያና አሜሪካ ከተማ ነው።
ባተን ሩዥ ወይም በፈረንሳይኛ አጠረር /ባቶን ሩዥ/ ማለት «ቀይ በትር» ነው። ፈረንሳዮች መጀመርያ በደረሱበት ጊዜ (1691 ዓም)፣ ቀይ እንጨት ምሰሶዎች በምድር ተሳክተው አገኙ፣ ይህም የሁለት ብሔሮች የሁማ እና የባዩጉላ ብሔሮች ደንበር ለማመልከት ነበርና። በኋላ በ1713 ዓም ምሽግ በዚህ ሠፈር መሠረቱ።